Testo Enat - Fikeraddis Nekatibeb
Testo della canzone Enat (Fikeraddis Nekatibeb), tratta dall'album Misikir
ቢያልፍም ጊዜ ቢያልፍ፡ ዘመን ቢያልፍ አመታት
ቢያልፍም ጊዜ ቢያልፍ፡ ዘመን ቢያልፍ አመታት
የእምዬን ውለታ፡ የእምዬን የእምዬን
አልረሳም አልረሳም፡ በእድሜ ዘላለም
የእምዬን ውለታ፡ የእምዬን የእናቴን
አልረሳም፡ አልረሳም፡ በእድሜ ዘላለም
ፅናቱን ካደላት፡ እህህም፡ ትግስትን ተላብሳ፡ አሃሃ
ቀን ታሻግራለች፡ እህህም፡ በጨለማ ዳብሳ፡ አሃሃ
ልፋቷን ቆጥሮላት፡ አሃሃ፡ ይሰማታል ጌታ እህህም
አልፋ ታኖራለች፡ እህህም፡ ምርቃቷን ትታ
ምን የሚገርም፡ አለ ከእናት ጥበብማ?
አንጀቷ ደሞ አይችልም፡???
ጥሬውን አልማ፡ ደረቁን ፈጭታ
አርጋ አሳዳጊ ናት፡ ያላትን ፈትፍታ
ቢያልፍም ጊዜ ቢያልፍም፡ ዘመን ቢያልፍ አመታት
ቢያልፍም ጊዜ ቢያልፍም፡ ዘመን ቢያልፍ አመታት
የእምዬን ውለታ፡ የእምዬን የእምዬን
አልረሳም፡ አልረሳም፡ በእድሜ ዘላለም
የእምዬን ውለታ፡ የእምዬን የእናቴን
አልረሳም በእድሜ ዘላለም
እህህምም
የዚህ አለም እናቶች፡ እህህም፡ ቢለያይ ኑሮአቸው፡ አሃሃ
ሲያረግዙ፣ ሲያምጡ፣ አሃሃ፡ ሲያጠቡ አንድ ናቸው፡ እህህም
እንኳን የሰው እናት፡ እህህም፡ የአራዊት የወፏ፡ አሃሃ
ልጅ ታሳድጋለች፡ እህህም፡ የአፏን ሰጥታ በአፏ፡ እህህም
ለራስሽ መች ሆነ፡ ቆርሰሽ የጎረስሽው
ስም ተረፈሽ እንጅ፡ በጡትሽ ላኖርሽው
በክንዶቿ ታቅፈን፡ በፍቅር ያለምነው
ወተት ብቻ አይደለም፡ የህይወት አስትንፋስ ነው
ከሆድሽ ስወጣ፡ መች ነበረኝ ጉልበት
አይኔን ሳይገለጥ፡ በአይንሽ ያየሁበት
አቅፋም አሳድጋ፡ መች ሰከነ ልቧ
ልጇን ይከተላል፡ የማያርፈው ቀልቧ
የማያርፈው ቀልቧ፡ የማያርፈው ቀልቧ
አይ 10 በማትሞላ፡ በአምስቷ ደቂቃ
ስለ እናት ለማውጋት፡ ስለ እናት ለማውጋት፡ ምንም ጊዜ አይበቃ!
Credits
Writer(s): Elias Woldemariam, Abebe Birhane, Yonas Abirha
Lyrics powered by www.musixmatch.com
Link
Disclaimer:
i testi sono forniti da Musixmatch.
Per richieste di variazioni o rimozioni è possibile contattare
direttamente Musixmatch nel caso tu sia
un artista o
un publisher.