Testo Chaw Tilina - Esubalew Yetayew
Testo della canzone Chaw Tilina (Esubalew Yetayew), tratta dall'album Chaw Tilina
ቀን ሲያልፍ አመረረች በቃ አትመጣም
አልቆባታል የፍቅሬ ጣዕም
ከእንግዲህ እኔም ልተው ከተወችኝ
ፍቅሬን ትታ ከረሳችኝ
በአደባባይ ቆሜ ስለምናት
ማሰብ ከብዶኝ እሷን ማጣት
ጭላንጭል ተስፋ እንኳ በእሷ ጉዳይ
የሚያሳየኝ በር ባላይ
ቻው ቻው ቻው ትልና ተሰናብታኝ ሄዳ
ደሞ ትመጣለች ካለ'ኔ አልችል ብላኝ
ቻው ቻው ትልና በቃህኝ በቃህኝ
ደሞ ትመጣለች ዓይንህ ላፈር ብላኝ
ኸረ ጉድ ናት
ዞሬ ከእግሯ ስር ስር ከደጃፏ
አይደለችም ልክ እንዳፏ
ስትመጣ ተቀባይ ሸኚ ስትሄድ
ሆኗል ልቤ አሽከር መንገድ
ምን እንደሚያለያየን አላውቅም
ስትመጣም አልጠይቃትም
መውደድ አስሮ ገዝቶ ለጉሞኛል
እንደ ግዑዝ አስቀምጦኛል
ቻው ቻው ቻው ትልና ተሰናብታኝ ሄዳ
ደሞ ትመጣለች ካለ'ኔ አልችል ብላኝ
ቻው ቻው ትልና በቃህኝ በቃህኝ
ደሞ ትመጣለች ዓይንህ ላፈር ብላኝ
ኸረ ጉድ ናት
ልቤን በ'ጁ ፍቅር እየዘወረው
ትንፋሽ ውስጤን እያጠረው
እኔ እያልኩ ለሰዎች አሸማግሉኝ
እሷ እያለች ውይ ገላግሉኝ
ከዚ ኃላ ብዬ ተገዝቼ
ስትርቅ ካ'ይኔ ስንት ዝቼ
ገብቷት ማጠፊያ መዘርጊያው ልቤ
አልውል በሷ እንዳሳቤ
አሄሄ አሃሃ
አሄሄ አሃ ሃ ሃ
ጎራ እያለች ስዘጋጅ
እንዳለምድ ሌላ ወዳጅ
ሃሳቤን ስትሄድ አስታኝ
ወይ ትታ አተወኝ ረስታኝ
ዳኙኝ አዋዩኝ 'ባካችሁ
የምታውቁ አፍቅራችሁ
እሷ ብልጥ የቆቅ ዘመድ
እኔ ያለኝ አንድ መውደድ
ቻል ቻል ቻል አድርጌው እንጂ
ባጣ ሰው አስረጂ
ቻው ቻው ብሎ የሄደ ሰው
መመለሱ ምነው?
ቻው ቻው ቻው ትልና ተሰናብታኝ ሄዳ
ደሞ ትመጣለች ካለ'ኔ አልችል ብላ
ቻው ቻው ትልና በቃህኝ በቃህኝ
ደሞ ትመጣለች ዓይንህ ላፈር ብላኝ
ኸረ ጉድ ናት
Credits
Writer(s): Muluken Melesse, Samuel Alemu
Lyrics powered by www.musixmatch.com
Link
Disclaimer:
i testi sono forniti da Musixmatch.
Per richieste di variazioni o rimozioni è possibile contattare
direttamente Musixmatch nel caso tu sia
un artista o
un publisher.