Testo Ande Ethiopia - Gigi
Testo della canzone Ande Ethiopia (Gigi), tratta dall'album One Ethiopia
️ ፩ ኢትዮጲያ️
የማንነቴ መለኪያ ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ
የሶስትሺ አመት እመቤት አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ
እቴ አንቺ የኔ ሙሽራ ሀገሬ እስኪ ልጠይቅሽ
ያገቡሻል ይፈቱሻል ያጩሻል አሁንም ድንግል ነሽ
ከክብርሽ በታች ወደቁነገስታት በፍቅርሽ ተነድፈው
ደናግላን መነኑልሽ አለምን ደስታቸውን ጥለው
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
እማማ እማማ
ዘመን አመጣሽ የዘር በሽታ
መድሃኒት አለው የማታ ማታ
ሀገር በወገን እንዴት ይረታ
ፍቅር በነገር እንዴት ይፈታ
ዘር ሳይለያየን ወይ ሀይማኖት
ከጥንት በፍቅር የኖርንባት
እናት ኢትዮጵያ ውዲት ውዲቷ
በጎጆ አያልቅም ሙሽርነቷ
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
እማማ እማማ
የማንነቴ መለኪያ ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ
የሶስትሺ አመት እመቤት አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ
እቴ አንቺ የኔ ሙሽራ ሀገሬ እስኪ ልጠይቅሽ
ያገቡሻል ይፈቱሻል ያጩሻል አሁንም ድንግል ነሽ
ከክብርሽ በታች ወደቁነገስታት በፍቅርሽ ተነድፈው
ደናግላን መነኑልሽ አለምን ደስታቸውን ጥለው
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
እማማ እማማ
የማንነቴ መለኪያ ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ
የሶስትሺ አመት እመቤት አንድ ናት ኢትዮጵያ ሀገሬ
እቴ ማነው የሞሸረሽ አስጊጦ እንዲ ያሳመረሽ
ያገቡሻል ይፈቱሻል ሀገሬ አሁንም ድንግል ነሽ
ከክብርሽ በታች ወደቁነገስታት በፍቅርሽ ተነድፈው
ደናግላን መነኑልሽ አለምን ደስታቸውን ጥለው
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
እማማ እማማ
ሀገር በውበት ወጥመድ ተይዛ
የዘመን ስቃይ ጭንቅ እንደ ዋዛ
እናት እራቆት እንዴት ልይሽ
ክብርሽ የታለ አንድነትሽ
አርበኛ አርበኛ አርበኛ አላይ
ልውጣ መቅደላ ልበል ዋይ ዋይ
ምነው ቢነሳ መይሰው ካሳ
አልወድም ጎበዝ ጀግና ሲረሳ
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
እማማ እማማ እማማ እማማ እማማ እማማ እማማ እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
ቃል የእምነት እዳ እንጅ ያባት የእናት አይደል
እማማ እናት ኢትዮጵያ
እማማ አንቺ እናት አለም
ቃል የእምነት እዳ እንጅ ያባት የእናት አይደል.
Credits
Writer(s): Gigi
Lyrics powered by www.musixmatch.com
Link
Disclaimer:
i testi sono forniti da Musixmatch.
Per richieste di variazioni o rimozioni è possibile contattare
direttamente Musixmatch nel caso tu sia
un artista o
un publisher.